top of page
0M1A4895.jpg

በዩኬ ውስጥ በሬማ እምነት አገልግሎት የተተከሉ አብያተ ክርስቲያናት 

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ክቡር ደሙ ተቤዥቶ የወለዳት ወደ ራሱ የጠራት ደግሞም ራስ የሆነላት የገሃንም (የሲኦል) ደጆች የሆኑት ሞትና መውጊያው የማይቋቋሟት ዓለሙን ከእግዚአብሔር  ጋር የማስታረቅ አገልግሎት የተሰጣት በእግዚአብሔር ሀይልና ሥልጣን ጸጋ የተሞላች በምድር የምትሰራ የክርስቶስ አካል ናት (ኤፌሶን 1፣15-23) 

ስለ ሬማ

DV5A4747.jpg

ስለ ሬማ እምነት አገልግሎት

የሬማ እምነት አገልግሎት መስራች እና መሪ መልእክት ሐዋሪያው ዘውዴ ገብረስላሴ

በክርስቶስ የተወደዳችሁ በፍቅር እና በደስታ ወደ ገፃችን እንኳን ደህና መጣችሁ ። እግዚአብሔር በሰጠን እውነተኛ ራዕይ የተጠነሰሰው እና የሚመራው ሬማ እምነት አገልግሎት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያገለግል የተልእኮ አገልግሎት ነው። ጌታ የወንጌልን መልእክት አደራ እንደሰጠን ጌታ በከፈተልን በሮች ሁሉ የወንጌልን መልእክት በማድረስ ላይ እንገኛለን። በቤተክርስቲያናችን በማህበረሰባችን የእግዚአብሔር የፍቅር መልእክት እና የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት ለማስተላለፍ ቁርጠኛ ከሆኑ አባላት፣ ቋሚ የራእይ ተካፋዮች እና የተባረከ የክርስቲያን ማህበረሰብ ጋር ጌታን በፍቅር እናገለግላለን። እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ዘላለማዊ ዓላማ ለመያዝ አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ እና በመፈጸም ራሳችንን ለጌታ የሰጠን አገልጋዮች ነን። የኢየሱስ ታላቁ ተልእኮ "እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤" (ማቴዎስ 28፡19-20) እንደመሆኑ መጠን የአገልግሎታችን አስኳል ይህንኑ ታላቁ ተልእኮን ያማከለ ሲሆን የወንጌል መልእክታችንም በቅንነት እና የማያመቻምች ነው፡

የዚህ የተባረከ የእግዚአብሔር አገልግሎት አካል ስለሆናችሁ ይህን አገልግሎት ስናካፍላችሁ በደስታ ነው። ከእናንተ ጋር እግዚአብሔርን ማምለክ እና ማገልገል ልባዊ ፍላጎታችን ነው። በመሆኑም ድረ-ገፃችን መረጃ ሰጪ፣ ጋባዥ እና አነቃቂ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ እናደርጋለን። በሁሉም መንገድ ሁል ጊዜ ለእግዚአብሄር ቃል መልእክት ልባችሁ ክፍት እንዲሆን እና የእግዚአብሔር መንፈስ ለልባችሁ እንዲናገር እንድትፈቅዱ ተስፋዬ እና ጸሎቴ ነው፡፡ በዚህ የእምነት ማህበረሰብ ውስጥ የፍቅር እና የመተሳሰብ ድባብ እንዲገጥማችሁ እና እንዲያድሳችሁ ነው። እግዚአብሔርን “በመንፈስና በእውነት” ለማክበር በየእሁዱ ለአምልኮ ከእኛ ጋር እንድሰበሰቡ እና አብራችሁን መንፈሳችሁን እንድታድሱ እንጋብዛችኋለን ፡፡ የእምነትን ጉዞ ከእርስዎ ጋር ለመካፈል እና ጌታን በአንድነት ለማክበር በጉጉት እንጠብቃለን። ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።

የላቀ ወሰን

የሬማ እምነት አገልግሎት በዩናይትድ ኪንግደም እና በዓለም ዙሪያ አያሌ አብያተ ክርስቲያናት ኔትወርክ ያለው ኤፍሲሲ FCC (Fellowship of churches of Christ) የክርስቶስ አቢያተ ክርስትያናት ህብረት ንቁ አባል ሲሆን የአገልግሎቱ መሪዎች በህብረቱ ከፍተኛ አመራር በቦርድ ዳይሬክተርነት ያገለግላሉ፡፡ ይህ ሁሉ ታዲያ የተጀመረው በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ኮንፈረንስ ሲያገለግሉ የቤተክርስቲያን በር ጠባቂ ለሐዋርያው ዘውዴ “በራእይ ሆድህ እጅግ ተዘርግቶ አየሁ፡፡ ጌታ ከምእራብ አፍሪካ እስከ ህንድ ድረስ ሄዳችሁ ብዙዎችን እንድትቆጣጠሩ ሰጥቷችኋል።” ሲል ትንቢት በመናገር ራእዩን ካፀና በኋላ ነው። ራዕያችን የመንግስቱን ሰራተኞች ለመጪው መኸር ማዘጋጀት እና ማስታጠቅ ነው። በቃሉ እንደምናስተውለው እና በታሪክ እንደታየው ታላቅ መከር እና መነቃቃት እየመጣ ነው። ኢየሱስ “አባቴ እኔን እንደ ሾመኝ . . . ለመንግሥት እሾማችኋለሁ።” (ሉቃስ 22፡29) በማለት እግዚአብሔር ስለ መንግሥት አደራ ሰጠን። መቼም በመንግሥቱ አስተሳሰብ ውስጥ በተመላለስን ጊዜ ሁሉ በዙሪያችን ተጽእኖ መፍጠር እንችላለን። በውጤቱም በዙሪያችን ላለው ዓለም ህያው ምስክር እንሆናለን እና በታሪክ ውስጥ የወንጌል አሻራን ትተን እናልፋለን። ይህ ሊሆን የሚችለው እኛ በእግዚአብሔር ቃል ስንኖር እና እንደ ቃሉ የመመዘኛ ደረጃ የሚኖሩ ሰዎችን ማፍራት ስንችል ብቻ ነው። ስለዚህ ለእግዚአብሔር ሰዎችን እናፈራ ዘንድ እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ደስ በማሰኘት አንመላለስም። ሰዎች በእግዚአብሔር ፍቅር የሚያድጉ ፣በእውነት የሚመላለሱ እና በዓላማ የሚኖሩ እንዲሆኑ እንተጋለን። ስለዚህም "ቃሌን ስሙ፥ እኔ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ አድርጉላቸው፤ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ" የሚለው አላማ መሪ ቃላችን ነው። በዚህ መሠረት ላይ የምንገነባው እንደ ምድራዊ ጥበብ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ሕያው ቃል ነው።

ተልዕኳችን

በሬማ እምነት አገልግሎት እግዚአብሔር ህዝቡን ሁሉ እንደሚቀባ እና እያንዳንዱን ለዓላማው እንደሚጠቀም እንጂ ቅባቱ በጣት ለሚቆጠሩ ለጥቂቶች ብቻ እንዳልሆነ እንገነዘባለን። በዚህ መሰረት እግዚአብሔር በሰጠን ራእይ መሰረት ለአንድ ዓላማ የሚቆም አንድ አማኝ ማህበረሰብ ለመገንባት እየሰራን ነው። ስለዚህም የተልእኮአችን መግለጫ “ክርስቶስ ኢየሱስን ለማወቅና ለመግለጥ በአንድ አሳብ፣ በአንድ ልብ፣ ለአንድ ዓላማ እንተባበራለን” የሚል ነው። ዓላማችን ክርስቶስን የሕይወታችን ማዕከል ማድረግ ስለሆነ ምንም ልዩነት ይኑረን በአንድ አሳብ እና በአንድ ልብ መስማማት እንደምንችል እናምናለን። በእግዚአብሔር የተጣለብንን ታላቅ ሃላፊነት ለመወጣት እና አላማውን ለመፈፀም ካለንበት ማህበረሰብ ጀምረን ወደ አለም ሁሉ በመሄድ የጠፉትን በክርስቶስ ፍቅር የምንደርስ እና የክርስቶስን ደቀ መዛሙርት የምናደርግ ህዝቦች እንድንሆን የሚያስችለን ይህ የአላማ አንድነት ብቻ ነው። ለግል ጥቅማቸው ሳይሆን እንደ ተስፋ ቃሉ ለእውነት የሚቆሙ እና ለክርስቶስ የሚኖሩ ሰዎችን ማስነሳት እና ማዘጋጀት አላማችን ነው፡፡ እንዲሁም በዓለማዊ ጥበብ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና እና በማይለወጠው የእግዚአብሔር ፍቅር የወንጌልን እውነት ሳናመቻምች በመግለጥ የጠፉትን መድረስ የጋራ ግባችን ነው

ቤተ ክርስቲያን

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ክቡር ደም ዋጅቶ ወደ ራሱ ጠርቶ የገሃነም ደጆች ራስ በማድረግ ቤተክርስትያንን በጣሩ የወለዳት የክርስቶስ የአካል ክፍል ነች።

አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን

ቤተ ክርስቲያን ዳግም የተወለዱና አንድ እምነት ያላቸው ቅዱሳን ለአምልኮ፣ ለጸሎት ፣ ቃሉን ለማጥናት እና የምሥራቹን ወንጌል ላልሰሙት የሚሰብኩበት ህብረት ነው። የአጥቢያ ቤተክርስትያን ህብረት እርስ በርሳችን የምንታነጽበት እና የጸጋ ስጦታን የምንካፈልበት ጉባኤ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያዝዘው በፍቅር እና እግዚአብሔርን በመፍራት ከሁሉም ጋር በሚገባ በመመላለስ ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ ሙላት ለመድረስ በግል እና በጋራ ራሳችንን የምንቀርጽበት ህብረት ነው

ስለ አገልግሎቶቻችን የበለጠ ለማወቅ

እናመሰግናለን

© R H E M A   F A I T H   M I N I S T R I E

bottom of page