top of page

የአምልኮ  አገልግሎት “እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፥ ምስጋናውንም ዘወትር በአፌ ነው።

 

መዝ 34፡1 

Gospel Music
Praise and Hands Raised

የአምልኮ  አገልግሎት 

የክርስቲያኖች ህይወት የተመሰረተው በውዳሴ ላይ ነው ስለዚህ ውዳሴ የሁሉ ነገር መክፈቻ ነው ለዚህ ነው መጽሀፍ ቅዱስ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ የውዳሴ ህይወት እንዲኖረን ነው የሚያስተምረው ። የክርስቲያኖች ከፍተኛ ስራ ለእግዚአብሔር ሰሩ የሚያሰኛቸው በውዳሴ ህይወት ውስጥ ሲገቡ ብቻ ነው ለእግዚአብሔር ትልቅን ስራ መስራት ትፈልጋለህን? ዘወትር ወድሰው! አንድ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ህይወቱ አድጎአል የሚያስኘው በውዳሴ ህይወት ውስጥ ሲገባ ብቻ ነው።
 
“መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ አሳፍና ኤማን ኤዶታምም ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም፥ ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽልና በገና መሰንቆም እየመቱ በመሠዊያው አጠገብ በመሥራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእነርሱም ጋር መቶ ሀያ ካህናት መለከት ይነፉ ነበር። ካህናቱም ከመቅደሱ በወጡ ጊዜ፡ መለከቱንም የሚነፉ መዘምራኑም በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ። እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ እያሉ በአንድ ቃል ድምፃቸውን ወደ ላይ ከፍ አድገው በመለከትና በጸናጽል በዜማም ዕቃ ሁሉ እግዚአብሔርን ባመሰገኑ ጊዜ፥ ደመናው የእግዚአብሔርን ቤት ሞላው። ዜና 5:12-13
 
ቤተክርስቲያን የአምልኮ  የአገልግሎት ዓላማ
 
በክርስቶስ በኩል የእግዚአብሔርን ማንነት በመንፈስ ቅዱስ ሃይል አማካይነት እንዲገለጥ፣ ጉባኤው የእግዚአብሔርን ማንነት በመረዳት እንዲያወድሰው፣ ማዳኑን እንዲመሰክር እና ህልውናውን እንዲያጣጥም በዝማሬ ማነሳሳት ነው። 
 
የሰዎች መንፈስ እግዚአብሔርን ለማምልክና ለማክበር እንዲነሳሳ ጉባኤውን በዝማሬ መምራት፣  በጉባኤ መካከል ከዝማሬ አገልግሎት የተነሳ እግዚአብሔር ሲከብር ማየት፣  ቅዱሳን እግዚአብሔርን ለማክበር ልባቸው ሲነሳሳ ማየት፣ በጉባኤ መካከል ከዝማሬ አምልኮ የተነሳ እግዚአብሔር በብርታት እንዲገለጥና በርሱ መገለጥ  (መገኘት) የሰዎች ሕይወት ወይም ሁኔታ ሲለወጥ ማየት፣

ስለ አገልግሎቶቻችን የበለጠ ለማወቅ

እናመሰግናለን

© R H E M A   F A I T H   M I N I S T R I E

bottom of page