
የልጆች አገልግሎት እና ዓላማ
የልጆች አገልግሎት እና ዓላማ
”ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለም ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም”
ሕጻናትና ልጆች የቤተክርስቲያንና እንዲሁም የትውልድ የወደፊት ተስፋ እንደመሆናቸው መጠን እነርሱን በእግዚአብሔር ቃል በመኰትኮት በቀጣይ ዘመናቸው ለሚኖራቸው መንፈሳዊ ህይወት መሰረት የሚጣልበትና በመንፈስ ማሳደግ የአገልግሎቱ ተቀዳሚ ዓላማ ነው።
የአገልግሎቱ ድርሻ
ሕጻናትና ልጆችን በሰንበት ትምህርት ለዚሁ አገልግሎት በተሰጡ የቤተክርስቲያኒቷ አገልጋዮች በኩል ጤናማ የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል (መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት )እየተገነዘቡ እና እየጨበጡ እንዲያድጉ ለማድረግ በተለያየ የማስተማር ዘዴ እንዲማሩ ይደረጋል።
ሕጻናትና ልጆች የቤተሰብ አካል እንደመሆናቸው መጠን ይህ አገልግሎት ጤናማ ቤተሰብ ለማፍራትም ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያበረክታል፤ ወላጆችም በአምልኮ ቀን ከልጆች ጋር ባላቸው ነገር ተጠምደው እንደሚገባ ማምለክ ስለማይችሉ የአገልግሎቱ መኖር ከልጆችም አልፎ ወላጆቻቸውንም የሚያሳርፍ አገልግሎት ነው፤ በየሳምንቱ ባለው የአገልግሎት ቀን ልጆች ምግብና መጠጥ እንዲያገኙ የአገልግሎቱ ክፍል አስፈላጊውን ድርሻ
ይወጣል።
በልጆች ህይወት እግዚሃብሄር አላማ እንዳለው ማመን ወደፊት የእግዚሃብሄር መንግስት ሰራተኞች እንደሚሆኑ መጠን በዚህ እምነት ልጆችን ማስተማርና መቅረፅ።